መስከረም ሲጠባ፤ያነጫንጭ ይሉ
መስከረም ሲጠባ፤ያነጫንጭ ይሉ፡
ነፍስ ምናፍስቱ ቢሉም ይቀርባሉ ፡
የኔውስ ቆየበት ሰንበት ብልዋል አሉ።
እናም፡ማልቀስ ማለቃቀስ እንዴት ላቁም እኔ፤
ልቀጥል ልቀጣጥል ላስተውል በውኔ
ይሞላልኝ እንደሁ፤እስኪያልፍልኝ ቀኔ።
-
እንቁ፡ ጣጣሽ ይሉ፤ ነጋልን ፈካልን የአደዩ አበባ፤
አውዳመት ቢመጣ፣ ቢወዱት፤ቢወደት፣ መስከረም ቢጠባ
ታዲያስ ምን ይጠበስ፤ የኔ አይደል የደራው፤
ልቀጥል ልቀጣጥል ላስተውል በውኔ
ይሞላልኝ እንደሁ፤እስኪያልፍልኝ ቀኔ።
-
እንቁ፡ ጣጣሽ ይሉ፤ ነጋልን ፈካልን የአደዩ አበባ፤
አውዳመት ቢመጣ፣ ቢወዱት፤ቢወደት፣ መስከረም ቢጠባ
ታዲያስ ምን ይጠበስ፤ የኔ አይደል የደራው፤
የኔማ ጥኔ ነው፤ በሚሊዮን መንደር ምዓት ከመከራው።
ረሃብና ችግር ማምረቱ አንሷቸው!
ቆሽቴ እየበገነ ሁሉን ሳሳልፈው፡
ከፈለግህ ደግሞ ይባስብህ ብለው ፤
ሳር ቅጠሉን ሁሉ አሸባሪ ብለው
ከፈለግህ ደግሞ ይባስብህ ብለው ፤
ሳር ቅጠሉን ሁሉ አሸባሪ ብለው
እውነት ከዳሚውን ኣፉን አስለጉመው
ተጫዋችም ሳይቀር ቁምነገር ከልክለው፤
በደበበ እሸቴ፦ ፈገግ ብለን እንኳን ጊዜን እንዳንገፋው፤
ተስፋና ፈገግታ እንዳይኖር ደንግገው፤
አርዓያ፦ ለነጻነት ድፍረት እንዳይሆኑ ነፍገው
ጎበዝ! እስክንድር ፤ አንዷለምን አይቶ፦ ልቡን እንዳይሞላ ፈርተው
መላ ሃገሩን ሁሉ፦ ቆርጠዋል ሊያደርጉት፦ ወህኒ ቤት ቀዝቃዛው!
ከህሊና ቢስ ሌላ፦ ኧረ ለመሆኑ ፦ዛ ሬ ! ማን አል የሚሞቀው?
እንግዲያስ ወዳጄ፤ በየትኛው ታምር መነጫነጭ ልተው፤
አንገት አቀርቅሮ ልብ ሀሞት ሲጎድለው። እንግዲያስ ወዳጄ፤ በየትኛው ታምር መነጫነጭ ልተው፤
-
እንዲያው ፤ አልፎም ተርፎ፤
ወዳኛውን ባየው፣ ባምነው ብዘከረው
ለዚህኛው ምድር፤ አልበጀኝ፤ ሆዴንም፣ ልቤንም አልሞላው።
ደሞስ- ሃይማኖቱ ሁሉ የኖሩበት ሃገር በክብር ተሳስበው፤
ሼክ አይቀር ፓፓሱ ይባሉበት ዘመን ሆነና እንደ ሰው
ምንፈሱም ርቆናል ምድር ባዶውን ነው፡፡
-
ደግመን ድጋግመንም፤ጠብበን፤ ነገሥነው፡
ገዛነው እያሉን፤እነሱም እነዚያም ቢተረክላቸው፤
እንዲያው ከፍ ፤ክፍፍ ያለውም ሰም፣ ባፋፍ ባፋፉ ላይ ቢስየምላቸው፤
የኔን ቤትስ ፤ ተዉት፤ ቢሞላ ባይሞላ፡ቢነከር በእዳ
መላ-ሃገር ሁሉ ፡ ተላንትናም ዛሬ አረጉት የባዳ፤
እነደ መነደራቸው፤ የጨርቃ ጨርቅ ገቢያ
ቸርችረው በተኑት ላሞራው ቅኝ ገዢ፤ ባህር ማዶ ወዲያ ።
*
እንዲህ ሆኖ እኮ ነው፣ መስከረም ሲጠባ፤ይሚያመናጭቀው፤
ከንገዲህስ በቃን እኒንም እኒያን ውጊድ እንበላቸው።
እነደ መነደራቸው፤ የጨርቃ ጨርቅ ገቢያ
ቸርችረው በተኑት ላሞራው ቅኝ ገዢ፤ ባህር ማዶ ወዲያ ።
*
እንዲህ ሆኖ እኮ ነው፣ መስከረም ሲጠባ፤ይሚያመናጭቀው፤
ከንገዲህስ በቃን እኒንም እኒያን ውጊድ እንበላቸው።
ቢሆንም ባይሆንም፣ የሆነም ሆኖ ፤የማይሆንም ቢሆን፤
ህይወት ትልቃለች፤ ብታምርም፣ ብትመርም፣ ብትቀጥን፤
እንደ የወጋችን፤ እንደየምነታችን፣
እስኪ ይሁን፤ መልካም ፣ ሰላም ዓመት፤እንዳው ለሁላችን።
*
ሲሆ ን ቢሆንማ ንጭንጭ ማጉረምረሙን ትተን
ነበር እንደሰዉ ከንቁ ጣጣሽ አልፈን ማክበር ዳመራውን!
*
ሲሆ ን ቢሆንማ ንጭንጭ ማጉረምረሙን ትተን
ነበር እንደሰዉ ከንቁ ጣጣሽ አልፈን ማክበር ዳመራውን!
No comments:
Post a Comment