TOP

Friday, 10 September 2010

መልካም ዓመት...Happy New Ethiopian Year

መስከረም ሲጠባ፤ያነጫንጭ ይሉ *1









:-( መስከረም ሲጠባ፤ያነጫንጭ ይሉ፡
ነፍስ ምናፍስቱ ቢሉም ይቀርባሉ
የኔውስ ቆየበት ሰንበት ብልዋል አሉ።

እናም፡ማልቀስ ማለቃቀስ እንዴት ላቁም እኔ፤
ልቀጥል ልቀጣጥል ላስተውል በውኔ
ይሞላልኝ እንደሁ፤እስኪያልፍልኝ ቀኔ።
-
እንቁ፡ ጣጣሽ ይሉ፤ ነጋልን ፈካልን የአደዩ አበባ፤
አውዳመት ቢመጣ፣ ቢወዱት፤ቢወደት፣ መስከረም ቢጠባ
ታዲያስ ምን ይጠበስ፤ የኔ አይደል የደራው፤
የሰዉ ሰው ቤት ነው፣ ዛሬም የሚሞቀው፡
እንግዲያስ ወዳጄ፤ በየትኛው ታምር መነጫነጭ ልተው።
-
እንዲያው አልፎም ተርፎ፤
ወዳኛውን ባየውባምነው ብዘከረው
ለዚህኛው ምድር ፤አልበጀኝ ፤ሆዴንም፣ ልቤንም አልሞላው።

የምድር ቤተ-መቅደስ፣ ነገሥታቱ ምንጭ፣ሲባል ከሚጠራው፤
ዘነዶ አወጣ እንዲሉ፣ የአሣ ጎርግዋሪው፤
ዘሬን ቆጣጥሬ፣ ተመረጥኩኝ ብዬ ፣ከማዶም ማዶውን፣ ባህር ተሻግሬ
ከስር ምሰረቱ፤ከቤተ እሥራኤልም፣መኖሬን ጀምሬ፤
ይባስ ...ገና ይገርምሃል፣ ትቃጠልአረህ ፣ትደብናለህ ብለው፤
አሽቀንጥረው ጣሉኝ ጠቅዋቁሬባቸው።
-
ደግመን ድጋግመንም፤ጠብበን፤ ነገሥነው፡
ገዛነው እያሉን፤እነሱም እነዚያም ቢተረክላቸው፤
እንዲያው ከፍ ፤ክፍፍ ያለውም ሰም፣ ባፋፍ ባፋፉ ላይ ቢስየምላቸው፤
የኔን ቤትን ተዉት፤ ቢሞላ ባይሞላ፡

መላ-ሃገር ሁሉ ተላንትናም ዛሬባዶም የባዳ ነው።

እንዲህ ሆኖ እኮ ነው፣ መስከረም ሲጠባ፤ይሚያመናጭቀው፤
ከንገዲህስ በቃን እኒንም እኒያን ውጊድ እንበላቸው።


ቢሆንም ባይሆንም፣ የሆነም ሆኖ ፤የማይሆንም ቢሆን፤
ህይወት ትልቃለች፤ ብታምርም፣ ብትመርም፣ ብትቀጥን፤
እንደ የወጋችን፤ እንደየምነታችን፣

መልካም ሰላም ዓመት፤ይሁን ለሁላችን።

*


( *1 አዲስ ዓመት ሲገባ ያነጫንጫል ለሚል ወዳጅ ሁሉ

እንዲሁም በምድረ እሥራኤል በዘር መድሎ ለሚስቃዩ ፈላሻ ኢትዮጵዊያን የታስብ። ..)

No comments:

Post a Comment